Home 100 Days Performance Report
ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡
የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ፣ ስነምግባርና ምክንያታዊነትን ማሳደግ |
74% |
---|---|
በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ጥያቄዎችን በሰላማዊና በአግባብ የማቅረብና ምላሽ የማግኘት፣ እንዲሁም የምክንያታዊነት ባህል እየተፈጠረ ይገኛል |
የከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ጥራትና ተገቢነት |
89% |
---|---|
የትምህርትና ሥልጠና ተገቢነት ለማሳደግና የፕሮግራሞች ኦዲት ለማሻሻል ያለው ተቋማዊ አቅም እየጎለበተ ይገኛል |
ተቋማትን በልህቀትና ትኩረት መስክ ማደራጀት |
100% |
---|---|
ተቋማትን በተልዕኮ ትኩረትና በተዋረድ ለመለየት የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ የመለያ መስፈርትና ማስተግበሪያ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ከአመራር ጋር የጋራ ውይይት እየተደረገ ይገኛል |
የሥራ ፈጠራንና የምሩቃንን የመቀጠር እድል የሚያሳድጉ አደረጃጀቶችና ሥርዓት መዘርጋት |
71% |
---|---|
ከኢንደስትሪ ጋር በተፈጠረ ትስስርና ትብብር ወደ ንግድ የተቀየሩ ሃሳቦች እየጨመሩ መጥተዋል፤ እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን ጋር ያለ ትስስር እያደገ መጥቷል |
የሳይንስና ሳይንሳዊ አሰራሮችን ማጠናከርና መገንባት |
56% |
---|---|
የሳይንሳዊ ምርምሮችን ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችና የስነ-ምግበር መመሪያ ተዘጋጅቷል |
አለም አቀፋዊነትና አጋርነትን ማሳደግ |
79% |
---|---|
የትምህርት ተቋማትንና የሴክተሩን አለማቀፋዊነትንና ትብብርን ማሳደግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል |
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ | ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ | ቀጣይ አቅጣጫዎች |
---|---|---|
• ተቋማትን በተልዕኮ ትኩረትና በተዋረድ ለመለየት የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ የመለያ መስፈርትና ማስተግበሪያ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ከአመራር የጋራ ውይይት እየተደረገ ይገኛል | • በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተግባር ልምምድ ማድረጊያና የሃሳብ ማበልጸጊያ (internship and incubation) ማዕከላት እንዲደራጁ/እንዲጠናከሩ ማድረግ ታቅዶ በ18 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተጀመሩ ስራዎች ቢኖሩም አፈጻጸሙ አነስተኛ ነዉ | • የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ለልማት ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ማስቻል። ለዚህም የተጠና ትስስር ከመንግስትና ከገበያው (ኢንዱስትሪው) ጋር መፍጠር ያስፈልጋል • በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በጤና ባለሙያዎች እየተነሱ ያሉ የጤና ትምህርት ዘርፍ ካሪኩለም አፈፃፀም ችግሮችን በትኩረት ፈትሾ ከጤና ሚኒስትር ጋር በጋራ መፍታት ቢቻል • ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር የሀገሪቷን የወደፊት የሰው ሃይል ፍላጎት መተንበይ እና የከፍተኛ ትምህርት ተገቢውን የሰው ሃይል ስብጥርና ቁጥር እንዲያፈራ አድርጎ መቅረጽ • የሚኒስቴር መ/ቤቱን የሪፎርም ተግባራት ተቋማዊ ቅርጽ መስጠት |