የጤና ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የማህበረሰብ ተሳትፎ እና ባለቤትነት ማርጋገጥ፣ የጤና አገልግሎት፣ ተደራሽነት ማጠናከር፣ የጤና አገልግሎት ጥራት ማሻሻል

85%

የቀዶ ህክምና ካልጀመሩት 48 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች 24 አገልግልት እንዲጀምሩ ማድረግ ታቀዶ ተፈጽሟል
በሁሉም ሀገሪቱ ውስጥ ላሉ እድሜአቸዉ 15 ወር ለሚሞላቸዉ ህጻናት የሁለተኛ ዶዝ ኩፍኝ (MCV-2) ክትባት በመደበኛ የክትባት መርሃግብር ማስጀመር ታቅዶ በጸጥታ ችግር ምክኒያት ሙሉ በሙሉ አልተከናወነም
በክልል ሆስፒታሎች የቀዶ ህክምና ወረፋ ከሚጠብቁ 8,000 ዜጎች ውስጥ 40% አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ ታቅዶ ተከናውኗል

ብቃት፣ ብዛትና ሙያዊ ስብጥሩ የተሟላ የሰው ሃይል እንዲኖር ማስቻል

84%

በአገር አቀፍ ደረጃ የ6,000 የወረዳ አመራሮች የአስተዳደርና አመራር ስልጠና መስጠት ታቅዶ አንድ ዙር ስልጠና ይቀራል
በ Leadership incubation program (LIP) for health ሰልጣኞችን በመቀበል ስልጠና ማካሄድ ታቅዶ ተጠናቋል

በቂ እና ዘላቂነት ያለው የጤና ፋይናንስ እንዲኖር ማድረግ

100%

ከለጋሽ ድርጅቶች 42.6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሰብሰብ ታቅዶ ከዛ በላይ ተሰብስቧል

በመረጃ ላይ የተመሰረተ የውሳኔ አሰጣጥና አፈጻጸም

100%

በሶስት የባህል መድሃኒቶች ላይ የምርት ፓኬጅ (production package) የማዘጋጀት ስራን አሁን ካለበት 41 በመቶ ወደ 65 በመቶ ማድረስ ታቅዶ ተከናውኗል

የጤና አስተዳደርና የጤና ቁጥጥር ስርዓት

83%

በሁሉም ክልሎች ከባዕድ ነገር ጋር የተቀላቀለ ምግቦች (እንጀራና በርበሬ) ላይ ጥናት በማካሄድና 40 ድንገተኛ አሰሳ ለማከናወን ታቅዶ ተከናውኗል
በሀገር አቀፍ ደረጃ 180 የመድሀኒት ችርቻሮ እና 75 የመድሃኒት አስመጪዎችና ጅምላ አከፋፋዮችን ሞዴል ማድረግ ታቅዶ ተከናውኗል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
• የቀዶ ህክምና ካልጀመሩት 48 የመጀመሪያ ድረጃ ሆስፒታሎች 24 አገልግሎት እንዲጀምሩ ማድረግ ታቀዶ ተፈጽሟል
• በቅርቡ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር በኩል የጤና ዘርፍ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር፣ የአሰራርና የአፈፃፀም ችግሮችን ለመፍታት የተደረገው ጥረት አበረታች ነው
• በአገር አቀፍ ደረጃ 50 የማህበረሰብ ፋርማሲዎችን ማቋቋም ታቅዶ 30 ብቻ ተቋቁሟል
• መደበኛ ህይወት አድንና መሰረታዊ መድሃኒቶች አቅርቦት 95% ማድረስ ታቅዶ 88% ደርሷል
• የጤና አገልግሎት (service delivery) ጥራትን በማሻሻል፣ የመድሃኒት ስርጭትን ማዘመን፣ መድሃኒት በበቂ ሁኔታ ለህብረተሰቡ መቅረቡን በማረጋገጥ የዜጎችን እንግልት መቀነስ ይስፍልጋል
• ሁሉን አቀፍ ከፍተኛ ሆስፒታል በመገንባት ወደ ውጪ ሃገር ለህክምና የሚሄደውን በሽተኛ ቁጥር መቀነስ ላይ በትኩረት ቢሰራ:: ይህ የውጭ ምንዛሪ ፍሰትን ከመቀነስ በተጨማሪ የቱሪዝም ዘርፉን ያበረታታል ተብሎ ይጠበቃል
• ባለፉት መቶ ቀናት እቅድ የተለጠጠ ባለመሆኑ ከፍተኛ ውጤት ቢያስመዘግብም የህክምና ግበዐት፣ የሰው ሀብት ልማት እና ባጠቃላይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ከመስጠት ጋር የተያየዙ ለጤና ተቋማት የሚያስፈልጉ ስር ነቀል ለውጦች እንዲካተቱ ይምከራል
• በሚቀጥለው 100 ቀን እቅድ ውስጥ እነዚህን ቁልፍ ችግሮች ለመፍታት የሚደረግ እንቅስቃሴዎች በበቂ ሁኔታ እንዲፀባረቁ ይመከራል:: እንደሁም ከአሁኑ እቅድ በመማር የመስራት አቅምን ባገናዘበ መልኩ ከፍ ያሉ እቅዶችን ማቀድ ያስፈልጋል

የእርስዎ አስተያየት