የገቢዎች ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

ግንዛቤ መፍጠር

92%

ህጎችን ማጠቃለል፣ ማሻሻልና በድህረ ገጽ መጫን ታቅዶ በአብዛኛው ተከናውኗል

የአገልግሎት አሠጣጥ

75%

በወቅቱ የቅሬታ ምላሽ የሚያገኙ ግብር ከፋዮችን ብዛት ወደ 90 በመቶ አድጓል
ለሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ታቅዶ በዋና ዋና 4 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የግብር ከፋይ አገልግሎት ጥራት ላይ መካከለኛ ወይም ከፍ ያለ እርካታ ያላቸው ግብር ከፋዮች ብዛት ወደ 82 በመቶ አድጓል

ገቢ መሰብሰብ

97%

59.9 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 50.8 ቢሊዮን ብር (85%) ተሰብስቧል
የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ተጠቃሚዎችን ቁጥር አሁን ካለበት 82 በመቶ (160 ሺህ) ወደ 85 በመቶ (164ሺህ) ማሳደግ ታቅዶ 162 ሺህ (99%) ተከናውኗል

ለህግ ተገዢነትን ማረጋገጥ

82%

በህገ-ወጥ ተግበር ላይ ተሰማርተዉ ሃሰተኛ ደረሰኝ በሚጠቀሙ፣ ህጋዊ ያልሆነ የካሽ ሬጅስተር መሳሪያ ገዝተዉ ደረሰኝ በሚሰጡና በሚጠቀሙ እንዲሁም ያለአግባብ ተመላሽ በሚጠይቁ 45 ድርጅቶች ላይ እርምጃ መዉሰድ ታስቦ 135 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል

ምርትና ኤክስፖርት

66%

ከወጪና ገቢ እቃዎች የጉምሩክ ስነስርዓት ለመፈፀም ይጠየቁ ከነበሩት ሰነዶች ውስጥ ከእያንዳንዳቸው 40 በመቶ መቀነስ ሙሉ በሙሉ ተከናውኗል
በጉምሩክ ዋጋ አተማመን (ECVS) ዙሪያ ያሉ ችግሮችን የመለየት፣ የማስተካከል እንዲሁም ለማልማት የተያዙ ሥራዎችን ሙለ ለሙሉ መፈፀም ታቅዶ ጥናት ተካሂዷል

ሎጂስቲክስ

63%

የስካኒንግ ማሽኖችን ቁጥር ከ6 ወደ 8 ለመጨመር ታስቦ ከነባሮቹ 4 በመበላሸታቸውና ሊጠገኑ ባለመቻላቸው፣ አዳዲሶቹም አገልግሎት ላይ ባለመዋላቸው አጠቃላይ የማሽኖቹ ቁጥር ቀንሷል
የኤርትራ ወደብ አገልግሎት ለመጀመር 6 ጽ/ቤቶ ለመክፈት ታቅዶ 6ቱም ተከፍተዋል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
▪ ገቢን ከመሰብሰብ አኳያ ከባለፈው መቶ ቀን በላቀ መልኩ (97%) ተከናውኗል
▪ የታክስ መረብንና የግብር ከፋዩን አገልግሎት ጥራት መለካቱ ገቢን ዕድገት ለማፋጠን የሚደረገው እንቅስቃሴ ሚዛናዊ እንዲሆን ያግዛል
▪ በዛ ያሉ የህግ ማሻሻያ ሥራዎች ቢሰሩም በተጨባጭ ያመጡት ውጤት ካልተለካ እንደውጤት ማየት ያስቸግራል
▪ የግብር ከፋይ አገልግሎትን መለካት ቁልፍ ሥራ በመሆኑ ቀጣይነት ሊኖረው፣ በሁሉም ቅርንጫፎች ሊካሄድ እና እውነተኛ ተዓማኝነት ያለው መረጃ መሰብሰቡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል
▪ በቴክኖሎጂ በኩል የታቀዱት ድርጊቶች ያስገኙት ውጤት ዝቅተኛ ነው። ለምሳሌ የECVSን ችግሮች በመፍታት ረገድ
▪ በኦዲት እንደታየው የተገኘው ውጤት ከዕቅዱ በጣም ገዝፎ ሲገኝ የሥራው ጥራት ተጎድቶ እንዳይሆን መመርመር ይኖርበታል
▪ ህገ ወጥ የውጭ ንግድን አስመልክቶ ችግሮችን መለየት እንዲሁም ከማስተማርና ከማነቃቃት ውጭ ተጨባጭ እርምጃዎች ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትንም በተለይ ክልሎችን ማስተባበር ያስፈልጋል
▪ የታዩ የቴክኖሎጂ ችግሮችን ከመፍታት በተጨማሪ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ሥርዓትና ብቃት መገንባት ትኩረት ይሰጠው

የእርስዎ አስተያየት