የሰላም ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የሰላም ግንባታና ብሄራዊ መግባባት

85%

ሃገራዊ የሰላም ምክር ቤት በአዋጅ ማቋቋም ታቅዶ ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ለማፀደቅ ለሚመለከተው አካል ተልኳል
የሃገር ሽማግሌዎችን በመጠቀም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ማጠናከር ታቀዶ በሶስት አጎራባች ቦታዎች የእርቀ ሠላም ኮንፈረንስ ተካሂዷል
ስለሰላም የሚሰብኩ ጥበባዊ ስራዎችን ለመስራት ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል

የህግ የበላይነት ማስከበር

77%

ህገ ወጥ የጦር የመሳሪያ ዝውውር በተሰራው ማፕ መሰረት ፍሰቱንና ዝውውር ለመቀነስ ታቅዶ በ5 አካባቢዎች ልዩ ክትትል በማድረግ ህገ ወጥ የጦር መሣሪያዎችን የመያዝና እንዳይገቡ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነዉ
በየአካባቢው የተፈናቀሉ ዜጎችን በልዩ የዘመቻ ስራ 80% ወደ ቀያቸው መመለስ ታቅዶ ባጠቃላይ ከተፈናቀሉ 2.3 ሚሊዮን ዜጎች ዉስጥ 768,488 መመለስ ተችሏል። ተጨማሪ 1ሚሊዮን ተፈናቃዮች መመለስ ተችሎ የነበረ ቢሆንም ወደ 600,000 የሚሆኑት በተለያዩ ምክኒያቶች ተመልሰው በመፈናቀላቸዉ በድጋሚ ለማቋቋም ስራ ተጀምሯል

የፌደራሊዝምና አርብቶአደር ጉዳዮች

68%

የልዩ ድጋፍ ክልሎችን የልማት ክፍተት ለመሙላት በፌዴራል መንግስት የ450 ሚሊዮን ፕሮጀክት አተገባበር ውጤታማ ማድረግ ታቅዶ 79 ሚሊዮን ብር ለክልሎች እንዲደርስ ተደርጓል
በአርብቶአደር ማህበረሰብ በ2011 በእቅድ የተያዙ 300 ንዑሳን ፕሮጀክቶች ማጠናቀቅ ታቅዶ 327 ተቋማት ተጠቃሎ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ተደርጓል

የሞደርናይዜሽንና የስታንዳርዳይዜሽን ግቦች

70%

የፖሊስና የደህንነት ተቋማት ስታንዳርድ ጥናት አጠናቆ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ተከናውኗል
National Secured Communication System ጥናቱ አልቆ ወደ ስራ ለመግባት በመንግስት የበጀት ማፈላለግ ስራ ተጀምሯል
ብሔራዊ መታወቂያ፣ የጥሪ ማዕከል፣ የመሳሪያ ምዝገባ ማስተዳደሪያ ሲስተም ተግባራዊ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
• የፌደራልና የክልል መንግስታትን ግንኙነት ለማዳበር የተጀመሩ ስራዎች
• የእናቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶችን በማካተት የተጀመሩ የእርቀ ሰላም ስራዎች
• ‹‹ጉዞ ሉሲ ለሰላም›› ፕሮጀክት ጋር እስከአሁን በአራት ክልሎች መካሄዱ
• የእስልምና ሃይማኖት አመራሮች መካከል የነበረውን መከፋፈል ለመፍታት የተደረገው ጥረትና የተገኘው ውጤት
• ምቹ የስራ ከባቢ ከመፍጠር አንጻር መልካም ስራ ተሰርቷል
• ብሔራዊ መታወቂያ እና የጥሪ ማዕከል ፕሮጀክቶች መዘግየት
• የልዩ ድጋፍ ክልሎችን የልማት ክፍተት ለመሙላት በፌዴራል መንግስት የ450 ሚሊየን ብር ፕሮጀክት ታቅዶ 79 ሚሊዮን ብር ብቻ ለክልሎች መድረሱ
• የኮንትሮባንድ ንግድ (ህገወጥ መሳሪያ ቁጥጥርን ጨምሮ) ኢኮኖሚዉና የብሄራዊ ደህንነት ላይ ካለዉ አሉታዊ ተጽእኖ አንጻር የተሰራዉ ስራ በቂ አለመሆን
• የመሳሪያ ምዝገባ (ዳታ ቤዝ) የህገወጥ የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ስራ ላይ ከሚኖረዉ ጉልህ አስተዋጾ አንጻር ትኩረት ተሰጥቶት ቢሰራ። የሚያስፈልገዉን የቅድመ ዝግጅት ስራ አጠናቆ ግልጽ የሆነ የትግበራ እቅድ በማዉጣት ስራውን ማስጀመር
• በፌደራልና በክልል መካከል እና በክልሎች የጸጥታ አካላት መካከል ሊኖር የሚገባዉን የቅንጅት ግንኙነት እንዲሁም ስታንዳርድ ግልጽና ዘላቂ በሆነ መልኩ ለማስቀመጥ የተጀመሩ ስራዎች ቢኖሩም በቂ አይደሉም። ተቋሙ በዚህ ላይ ትኩረት በማድረግ የሚያስፈልጉ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ፣ መግባቢያ ሰነዶችን በማዘጋጀትና ተጨባጭ የቅንጅት አሰራር በመዘርጋት ላይ ቢያተኩር
• ግጭትን ለማስወገድ/ለመቀነስ የተለያዩ የዉይይት መድረኮችና ህዝቦችን የሚያቀራርቡ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉ የሚበረታታ ቢሆንም እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የእርቀ ሰላም ኮሚሽንና የወሰንና ማንነት አጣሪ ኮሚሽንን አጠናክሮ ወደ ስራ ማስገባት ያስፈልጋል። ስለዚህም ትቋሞቹን ወደሙሉ ስራ የማስገባት እቅድ ተይዞ ተግባራዊ እንዲያደርግ

የእርስዎ አስተያየት