Home 100 Days Performance Report
ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡
የመስኖ እርሻ ማስፋፋት |
85% |
---|---|
3.1 ሚሊዪን ሄ/ር መሬት በመስኖ መሸፈን ታቅዶ 2.2 ሚሊየን ሄ/ር መሬት በመስኖ ተሸፍኗል | |
በአዋሽ፣ ሸበሌና ኦሞ ተፋሰሶች በ3502 ሄክታር በመስኖ ከለማ የቆላ ስንዴ 14 ሺ ቶን ምርት መሰብሰብ ታቅዶ 15.4 ሺ ቶን ምርት ተሰብስቧል |
የሰብል ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እና ጥራት ማሻሻል |
38% |
---|---|
በበልግ ኩታ ገጠም ገበያ መር የሰብል ልማት 1.5 ሚ/ን ሄክታር በዘር መሸፈን ታቅዶ 0.4 ሚሊየን ሄክታር በዘር ተሸፍኗል | |
በሜካናይዜሽን የተጠቃሚ አርሶ አደር ቁጥር 3.2 ሚ/ዮን (20%) ማድረስ ታቅዶ 50% ስራው ተሰርቷል |
የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ |
79% |
---|---|
ስጋ 500 ወደ 1050.45 ሺህ ቶን፣ ቆዳና ሌጦ ከ9.41 ወደ 16 ሚሊዮን ለማድረስ ታቅዶ - ስጋ 900.8 ሺህ ቶንና ቆዳና ሌጦ ክንውኑ 18.1 ሚሊዮን ማድረስ ተችሏል |
የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ |
92% |
---|---|
ጥበቃ ስራዎች 1.12 ሚ/ሄ/ር፣ የዛፍ ችግኞች 3.75 ቢሊዪን ችግኝ፣ የገጠር የስራ ዕድል ለ939,394 ግለሰቦች መፍጠር ታቅዶ - 1.37 ሚሊየን ሄ/ር መሬት ሽፋን፣ 3.57 ቢሊየን ችግኝና 694,475 የሥራ ዕድል ተፈጥሯል |
የቴክኖሎጂ አቅርቦትና አጠቃቀምን ማሻሻል |
81% |
---|---|
አመታዊ የምርጥ ዘር አቅርቦት 1.2 ሚሊዮን ኩንታል ማድረስና 450,971 ኩንታል ማሰራጨት፣ የድሬደዋ ማዳበሪያ ፋብሪካን ለማቋቋም ሽርክና መፈራረም ታቅዶ 1.12 ሚሊየን ኩንታል ምርጥ ዘር ተሰብስቦ 189,094 ኩንታል ለበልግ እርሻ ለአርሶና አርብቶ አደር ቀርቧል |
የግብርና ኤክስፖርት ምርት አቅርቦት ማሳደግ |
56% |
---|---|
ከቁም እንስሳት ኤክስፖርት 83,690,745 ዶላር፣ ከቡና ምርት 725.6 ሚ/ን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ ከቁም እንስሳት 12,732,270 ዶላር፣ የቡና ምርት 164.90 ሚ/ን ዶላር ማመንጨት ተችሏል |
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ | ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ | ቀጣይ አቅጣጫዎች |
---|---|---|
•የእንስሳት ምርታማነትን ለማሳደግና የተፈጥሮ ሃብትን ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ እንቅስቃሴዎችና ቴክኖሎጂዎች ላይ ከባለፈው መቶ ቀን አፈጻጸም በተሻለ መልኩ ተሳክቷል •በመንግሥት ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው የቆላ ስንዴ ፕሮጀክት ላይ ቀጣይነት ያለው ውጤት ተገኝቷል |
•ካለፈው መቶ ቀን ጀምሮ በዝቅተኛ አፈጻጸም ላይ የሚገኙ መስኮች በተለይ የዘር አቅርቦት፣ ዓሳና የቁም እንስሳት ውጭ ንግድ ለየት ያለና ውጤታማ የሆነ ስትራቴጂ አልታየባቸውም •የግብዓት አቅርቦት እጥረት እያለ ከፍተኛ መጠን ያለው የአገልግሎት ጊዜው ያለፈ ብሎም ለማስወገድ የውጭ ምንዛሬ የሚጠይቅ የኬሚካል ክምችት መገኘቱ ሚ/ር መሥሪያ ቤቱ ብክነትን ለመቀነስ ጠንከር ያለ ሥርዓት አለመገንባቱን ያመላክታል |
•ከመደበኛ ሥራ ይልቅ የዘርፉን መሠረታዊ ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ የፖሊሲም ሆነ ሌሎች እርምጃዎች ተለይተው በመቶ ቀን ዕቅድ በትኩረት ተሠርቶባቸው አፈጻጸማቸው ሪፖርት ቢደረግ •ባለፈው መቶ ቀንም ሆነ በቀጣይነት በቀይ አፈጻጸም ደረጃ የታዩ የሥራ መስኮች ለየት ያለ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል። ለምሳሌ የዘር አቅርቦት |