የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በሚኒስቴር መ/ቤቱ የሚሰሩ ስራዎች

77%

የኢንኩቤሽን ማዕከላት እየለሙ የነበሩ 10 ቴክኖሎጂዎች በፕሮቶታይፕ ደረጃ ማስመረቅ ታቅዶ 2 ቴክኖሎጂዎች ተጠናቀዋል
ቦሌ ሌሚ2 እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ኢኖቬሽን ማዕከላትን ወደስራ ማስገባት ስራዎች በከፊል ተሰርቷል
የቴክኖሎጂ መንደርን ለማቋቋም የሰነድ ስራ አጠናቆ በሚኒስቴሮች ምክር ቤት ለማፀደቅ ታቅዶ አንድ የምስረታ ረቂቅ ሰነድ ተዘጋቷል
በቡራዩ በመሰራት ላይ ያለውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል ግንባታ ቢያንስ 50 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ 30 በመቶ ማድረስ ተችሏል
በሚኒስቴር መ/ቤት ከተደገፉት ምርምሮች የቴክኒክና ፋይናንስ ግምገማ ከነበረበት 50% ወደ 80% ማድረስ ተችሏል
ሀገር አቀፍ የፈጠራና የምርምር ዕውቅናና ማበረታቻ ስነስርዓት 180 ግለሰቦችን እና ተቋማት ተለይቷል

በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢኮቴ ዘርፍ የሚሰሩ ስራዎች

66%

የሀገሪቱ ዲጂታል ኢኮኖሚ የሚመራበትን ሁሉን አቀፍ አንድ አዋጅ አዘጋጅቶ ለመንግስት ውሳኔ ማቅረብ
ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የመንግስት የኢኮቴ ኢንፍራስትራክቸር የደህንነት ኦዲት ማስጀመርና ሪፖርት ማጠናቀቅ ስራ 15 በመቶ የሚሆነዉ ተሰርቷል
የተቀናጀ የመንግስት ኢኮቴ መሰረተ-ልማት (Integrated Government Network Infrastructure) ፕሮጀክት ዲዛይን 100% ተጠናቋል
አሁን በስድስት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተጀመረውን ኦንላይን የዲጂታል አገልግሎት መስጫ አፕልኬሽኖችንወደ 12 ለማድረስና የሙከራ ስራዎችን ማስጀመር ታቅዶ ስራዉ ተጠናቋል

በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሌሎች ሚኒስቴር መ/ቤቶች ጋር የሚሰሩ ስራዎች

77%

በግብርና፣ በጤና፣ ማዕድን፣ በንግድና በፋይናንስ፤ በኮንስትራክሽን ፣ በገቢዎች ፣ በኢነርጂ እና በትምህርት ዘርፎች የተሻለ አሰራርና ቅልጥፍናን ለማምጣት የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎችን አጥንቶ ለሚመለከታቸዉ ሚ/ቤቶች የማስረከብ ስራዎች በተለያዩ ደረጃዎች ይገኛሉ
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች

• ሚኒስቴሩ ባዘጋጃቸው ኢንኩቤሽን ማዕከላት አዳዲስ 30 ፈጠራ ያሏቸውን ወጣቶች የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዞችን ማስገባት
• ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋፆ ማድረግ የሚችሉ ተጨማሪ 15 ምርምሮችን በቴክኒካል ኮሚቴ መለየት፤
• በስድስት የመንግስት መስሪያ ቤቶች የተጀመረውን ኦንላይን የዲጂታል አገልግሎት መስጫ አፕልኬሽኖችን ማልማትና የሙከራ ስራዎችን ማስጀመር
• የደረሰውን የብሄራዊ ዳታ ማዕከል ዲዛዝተር ሪከቨሪ ማዕክል ዲዛይን 100% አጠናቆ ለበጀት ውሳኔ ማቅረብ፤

• በኢንኩቤሽን ማዕከላት ከነበሩ የቴክኖሎጂ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አስሩን ምርቶቻቸውን ፕሮቶታይፕ ማስጨረስና ማስመረቅ
• ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የመንግስት የኢኮቴ ኢንፍራስትራክቸር የደህንነት ኦዲት ማስጀመርና ሪፖርት ማጠናቀቅ
• በስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሥርዓተ ትምህርት ቀረጻ በታቀደዉ መሰረት አለመከናወኑ፣
• ከሌሎች የመንግስት አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራትና የስራ ድግግሞሽን ማስቀረት
• የሚለሙ ስርዓቶችና ሶፍትዌሮች በተጠቃሚው ፍላጎት መልማታቸውን ማረጋገጥ

• ታዳጊ ቢዝነስችን (Start up) ፕሮጀክቶችንና ኢንኩቤሽን ስራዎችን ሌሎች ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀትና ትኩረት ሰጥቶ በማበረታታት በዘርፎቹ ዉጤታማ ተጨባጭ እድገት ማስገኘት
• በመንግስትና የግል ሽርክና (PPP) በአዲስ አበባ የሚቋቋም “የቴክኖሎጂ መንደር” ስራ የሰነድ ስራዎች ተጠናቀዉ ወደ ስራ ይግቡ
• 2,2,2,2 ስትራቴጂ የደረሰበት ግልፅ በሆነ ሁኔታ ሪፖርት ይደረግ
• የዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት ሰላም ሚኒስቴር ከያዘዉ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጋር ተቀናጅቶ መሰራት ይኖርበታል። የሰላም ሚኒስቴር የዚህ ፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ ሆኖ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፕሮጀክቱን ዲጂታል ክፍል በመምራት የሚፈለገዉን ድጋፍ ቢያደርግ

የእርስዎ አስተያየት