የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የከተሞች የሥራ ዕድል ፈጠራና የምግብ ዋስትና

48%

በድምሩ 466 ሺህ የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ279,600 ስራ ፈላጊዎች ስራ ዕድል ተፈጥሯል

የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም

34%

የክልላዊ የከተማ ስፓሻል እና የክላስተር ፕላን ዝግጅት ለማስጀመር ታቅዶ፣ የቴክኒካል አማካሪ ለመቅጠር እየተገመገመ ነው

የከተማ መሬት ምዝገባ፣ አቅርቦትና አጠቃቀም

59%

90 ከተሞች የአስተዳደር ወሰናቸዉን እንዲያካልሉ ድጋፍ ማድረግ ታቅዶ 80 ከተማዎች ማካለል ተችሏል
በአዲስ አበባ 60ሺ የይዞታ በማረጋገጥ 54ሺህ ይዞታዎች የመብት ምዝገባ ለማካሄድ ታቅዶ 22,06 ተከናውኗል

የከተማ ቤት ልማትና አስተዳደር

67%

በክልሎች በሁሉም አማራጮች 40ሺህ ቤቶች ግንባታ እንዲጀመር ታቅዶ፣ ግንባታቸው የተጀመረ ቤቶች ቁጥር 44,123
በአአ የተጀመሩ 132 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በአማካይ 92 በመቶ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ ታቅዶ፣ 92 በመቶ የተጠናቀቁ ቤቶች ቁጥር 33,093

ደህንነቱ የተጠበቀና ተወዳደሪ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ

97%

አዲስ 25 የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ላይ ኦዲት በማድረግ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ውጤታማነት ለማሳደግ ታቅዶ ተከናዉኗል
በአንድ የመንግስት ህንፃ ፕሮጀክት ላይ የህንጻ መረጃ ሞዴል ትግበራን 100% ለማጠናቀቅ ታቅዶ፣ 70% ተጠናቋል

የተቀናጀ የከተሞች መሠረተ ልማት አቅርቦትና አስተዳዳር

95%

የፌዴራል 30 መሠረተ-ልማት ፕሮጀክቶችን አፈፃፀም ቀልጣፋና ብክነት እንዲቀንስ ለማድረግ ታቅዶ፣  ቅንጅታቸው የተረጋገጡ ፕሮጀክቶች በቁጥር 28
በፌደራል እና ክልሎች በጀት ድጋፍ በከተሞች  በድምሩ 4,262 ኪሜ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት ታቅዶ፣ የተገነቡየመሠረተ ልማቶች በኪ.ሜ. 3670

የከተሞች የአረንጓዴ ልማትና ጽዳት

53%

በ22 ከተሞች የደረቅ ቆሻሻ አሰባሰብና አያያዝ ሽፋን 86 ከመቶ እንዲደርስ ታቅዶ፣ 86 በመቶ የደረሱ ከተሞች ብዛት በቁጥር 15
የናማ ፕሮጀክት በ6 ከተሞች የሼድ ግንባታው ድጋፍ በማድረግ አፈፃፀሙ እንዲሻሻል ለማድረግ ታቅዶ፣ የተገነባ ሼድ ቁጥር 4

የከተማ የትራንስፎርሜሽን አመራር እና የከተሞች መልካም አስተዳደር

75%

በተመረጡ 11 የክልል ዋና ዋና ከተሞችና አአ ጨምሮ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት መሻሻሉን ከ40 በመቶ ወደ 60 በመቶ ለማድረስ ታቅዶ፣ በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት 60 በመቶ የደረሱ ከተሞች ብዛት 10
በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት 12,877 በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን በማሰልጠን የብቃት ማረጋገጫ እንዲያገኙ ለማድረግ ታቅዶ፣ የብቃት ማረጋገጫ ያገኙ ባለሙያዎች ብዛት7,547

የሲስተም ልማት ማጎልበት

100%

የህጋዊ ካዳስተር ሲስተም ልማት በከተማ ደረጃ ያለውን በማጠናቀቅ በ3 የክልል ከተሞች (ሐዋሳ፣ ባህርዳር እና አዳማ) በሙከራ ደረጃ እንዲተገበር ለማድረግ ታቅዶ፣ ትግበራ የተደረገባቸው ከተሞች ብዛት 3
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች

• በአዲሱ UIIDP የተካተቱት 73 ከተሞች የመሠረተ-ልማት ግንባታ ለማስጀመር የቅደመ ኢንቨስትመንት ሂደት መጠናቀቁ፣
•የህጋዊ ካዳስተር ሲስተም ልማት በከተማ ደረጃ ያለውን በማጠናቀቅ በ3 የክልል ከተሞች (ሐዋሳ፣ ባህርዳር እና አዳማ) በሙከራ ደረጃ እንዲተገበር መደረጉ፣
•80 ከተሞች የአስተዳደር ወሰናቸዉን እንዲያካልሉ ድጋፍ መደረጉ

•የከተሞች በምግብ ዋስትና ፕሮግራሙ በ11 ከተሞች የሚገኙ 141,115 ሺህ ዜጎች ተጠቃሚ ለማድረግ ቢታቀድም ተግባራዊ ያለመደረግ፣
•በክልሎች የክልላዊ የከተማ ስፓሺያል እና የክላስተር ፕላን ዝግጅት የግዥ ሂደቱን ማጠናቀቅና ለማስጀመር የታቀደዉ በሂደት ላይ መሆን፣
•የከተሞች የአረንጓዴ ልማትና ጽዳት ላይ የሚደረገዉ ክትትልና ድጋፍ አናሳ መሆን

•አንዳንድ የ2ኛ ዙር የ100 ቀን ግቦች አፈጻጸማቸዉ ዝቅተኛ በመሆኑ እነዚህን ግቦችን/ዕቅዶችን አስፈጻሚ ከሆኑ የከተማ አስተዳደርና ሌሎች ተቋማት ጋር የጋራ በማድረግ የሪፎርም እና የልማት ስራዎችን ተፈጻሚነት ለማረጋገጥ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ላይ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል
•አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የተቀናጀና የተሟላ አገልግሎት ከመስጠት አንጻር፣ በተለይ ለኢንተርፕራይዞች የማምረቻና የመሸጫ ቦታ አቅርቦት አናሳ መሆንና ለረጅም ጊዜ የተያዙትን በማስለቀቅ አዲስ ለተደራጁት የማስተላለፍ ስራዎች ዉስን በመሆናቸዉ በቀጣይነት ትኩረት ሊሰጠዉ ይገባል
•ተቋሙ በከተሞች ዉስጥ ያሉ የኮንስትራክሽን ስራዎችን ጥራትና የህግ ጥሰቶችን (ህገ ወጥ ግንባታን) መቆጣጠርና የከተማ ጽዳት ላይ ተጨባጭ ስራዎች ላይ እቅድ በማስቀመጥ በትኩረት መከታተል ያስፈልጋል

የእርስዎ አስተያየት