የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

ተደራሽ የመጠጥ ውሃ ሽፋንና ሳኒቴሽን አገልግሎት

89%

በአጠቃላይ ድሬዳዋ፤ ማይጪው፤ ገብረ ጉራቻ፤ ተፊኪ፤ ፊጋ ቆጶራ፤ ቶባ፤ ዲማ፤ አምበሳሜ፤ ኩታበር፤ ተንታ፤ አፍደራ ከተሞች ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ በድምሩ 607,772 ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
የሆለታ ከተማ የ200 ሜትር መስመር ዝርጋታ በወሰን ማስከበር ችግር ምክንያት ሳይጠናቀቅ ቀርቷል፡፡
በOne Wash የሚደገፉ 334 የገጠር መጠጥ ውሃ ተቋማት ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት በመጀመራቸው 112,647 ህዝብ ተጠቃሚ መሆን ችሏል
ብድር መመለስ ከጀመሩ ከተሞች /አዲስ አበባን ጨምሮ 68.8 ሚሊዮን ብር የብድር ተመላሽ ሂሳብ መሰብሰብ ታቅዶ 51.05 ሚሊዮን ብር ተገኝቷል

ፈጣንና ዘመናዊ የመስኖ ልማት

65%

የግድብ ግንባታ፡ አርጆ ዴዴሳ 66.8%፣ መገጭ 61% አና ዛሬማ ካለበት 91.5% ወደ 93.5% ደርሰዋል፤
የ41ሺ ሄክታር ኮሜርሻል መስኖ በወጣቶች ለማስጀመር ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ ወጣቶችም ተለይተው በስልጠና ዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡

የኢነርጂ ልማትና የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት

84%

የገናሌ ዳዋ ግድብ ውሃ ማጠራቀም ጀምሯል፤ በቅርቡ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ይጀምራል፤
የ1.8 ቢሊዮን ዶላር የኤሌክትሪክ ሽርክና ኩባንያው ስምምነት ተጠናቋል፤ የስቴትግሪድ ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልገውን ተጨማሪ ጥናት እያካሄደ ነዉ፡፡
77 የገጠር ከተሞች ውስጥ ለሚኖሩ ዜጎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተሰጥቷል፤

ዘለቄታዊና የተቀናጀ የተፋሰሶች ልማት፤ ውሃና ሜትሮሎጂ መረጃ

93%

160,543 ሄክታር ላይ ስነአካላዊና ስነሕይወታዊ አፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተሰርቷል
ለልማት የሚውሉ 7 የጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ተጠናቋል (100%) ሌሎች 7 ጉድጓዶች ቁፋሮ ተጀምሯል (66.67%)

ምቹ የሥራ አካባቢና ተቋማዊ አደረጃጀት

79%

የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን አደረጃጀት ተጠናቋል ፤የሁለቱ ኮሚሽኖችና አንድ ባለስልጣን አደረጃጀት ፀድቋል፡፡ የዋናው መ/ቤት በፐብሊ ክሰርቪስ ኮሚሽን እስኪፀድቅ ይጠበቃል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
• ዕቅዱ ሠፋ ያለና በርካታ አጋሮችን ያጠቃለለ ቢሆንም በአጠቃላይ በላቀ መልኩ ተከናውኗል።
• ክንውኑም በማኅበረሰቡ ተጨባጭ ኑሮ ላይ ግልጽ የሆነ መሻሻል የሚያመጡና በአሃዝ የተደገፉ ውጤቶች አሉት
• ሚ/ር መሥሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ድርጅቶች በተለይ ከገንዘብ ሚ/ር እንዲሁም ከገጠር ማኅበረሰብ ጋር ያለውን ትስስር ለማሻሻልና የፕሮጀክት መዘግየትን ለመቀነስ ጠለቅ ያለ ውይይት በማድረግ ስነልቦናዊ አብሮነት መገንባትና ማሻሻያ ስልት መቀየስ ይገባዋል • ዕቅድ ሲዘጋጅ የሚ/ር መሥሪያ ቤቱን አቅምና ዝግጁነት ብቻ ሳይሆን የሚመለከታቸው ድርጅቶችን አሠራር ባገናዘበ መልኩ ይሁን፤ ድርጊቶቹም የሚ/ር መሥሪያ ቤቱን ሚና የሚያመላክቱ ይሁኑ
• በተደጋጋሚ መዘግየትም ሆነ ዝቅተኛ አፈጻጸም የሚያደርሱ መሠረታዊ ምክንያቶች ተለይተው የመፍትሄ ሃሳብ ቢቀርብባቸው፤ በዋነኛነት በገጠር ማኅበረሰብና በፕሮጀክት ፈጻሚዎች መካከል የሚደረሱ ግጭቶች እንዴት እንደሚፈቱ፣ ከገንዘብ ሚ/ር አመራሮች ጋር ያለውን ቅንጅት በተለይ በጀትንና መግአ (PPP) ፕሮጀክቶችን በዘላቂነት ማቀላጠፍ እንዲቻል ከሚመለከተቸው ተቋም መሪዎች ጋር የአሠራር ማሻሻያ ላይ መስማማት ያስፈልጋል

የእርስዎ አስተያየት