የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የውጭ ምንዛሪና የሀገር ውስጥ ገቢን ማሳደግ

55%

በኩባንያዎች የተለያዩ ማዕድናትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪን ከ 5.251 ወደ 26.15 ሚሊየን ዶላር ማድረስ ታቅዶ፣ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ መጠን 5.98 ሚ. ዶላር
በባህላዊ እና አነስተኛ አምራቾች የተለያዩ ማዕድናትን ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ ከ 24.787 ወደ 50.787 ሚሊየን ዶላር ለማድረስ ታቅዶ፣ የተገኘው የውጭ ምንዛሪ መጠን 3.53 ሚ. ዶላር

የውጭ ምንዛሪ ማዳን

8%

የገቢ የፔትሮሊየም የሙከራ ምርት በማምረት 6.2 ሚሊየን ዶላር ለማዳን ታቅዶ፣ የዳነው የውጭ ምንዛሪ መጠን 0.467 ሚ. ዶላር

በዘርፉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ማሳደግ

56%

በኩባንያዎች የተፈጠረውን የሥራ ዕድል በቁጥር ከ 510 ወደ 1,852 ከፍ ለማድረግ ታቅዶ፣ የተፈጠረው የሥራ ዕድል 170
በዘርፉ በ6 ወራት በባህላዊ ማዕድን አምራቾች የተፈጠረውን የሥራ ዕድል በቁጥር ከ 50,654 ወደ 62,996 ከፍ ለማድረግ ታቅዶ፣ የተፈጠረው የሥራ ዕድል 126381

የሥነ-ምድር መረጃ ሽፋን ማሳደግና ዘርፉን በአለም አቀፍ ደረጃ ማስተዋወቅ

57%

በ1፡250,000 መስፈርት የሃይድሮ ጂኦሎጂ እና ኢንጂነሪንግ ጂኦሎጂ ካርታ ሽፋን በ2010 መጨረሻ ከነበረበት 983,891 ካ.ኪ.ሜ ወደ 1,098,341 ካ.ኪ.ሜ ለማድረስ ታቅዶ፣ ክንውን 18000 ካ.ኪ.ሜ ነበር

የአካባቢና የማህበረሰብ ልማት ገቢን ማሳደግና ለክልሎች ማስተላለፍ

55%

ከአልሚዎች ለማህበረሰብ ልማት የሚሰበሰብ ገቢ ወደ 12.1 ሚሊየን ብር ለማሳደግ ታቅዶ፣ የተሰበሰበው 25 ሚሊየን ነበር፤ ሆኖም ከዚህ ዉስጥ 6 ሚሊየን ብር ለክልሎች ለማስተላለፍ ታቅዶ የተከናወነዉ 600 ሺ ነዉ

ኢንቨስትመንትን መደገፍና ማስፋፋት

75%

የምርመራና የምርት ፈቃድ ወስደው ሥራ ያቆሙ 10 ኩባንያዎችን ወደስራ ለማስገባት ታቅዶ 15 ገብተዋል
የማዕድንና እና የፔትሮሊየም ፈቃድ 23 ለመስጠት ታቅዶ 12 ብቻ ተሰጥቷል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
• የአካባቢና የማህበረሰብ ልማት ገቢን ማሳደግ ከአልሚዎች ለማህበረሰብ ልማት 12.1 ሚሊየን ብር ለመሰብስብ ታቅዶ የተሰበሰበ 25 ሚሊየን ብር መሆኑ.
• በባህላዊ ማዕድን አምራቾች የተፈጠረውን በቁጥር 50,654 የሥራ ዕድል ወደ 62,996 ከፍ ማድረግ ታቅዶ የተፈጠረው የሥራ ዕድል 84,532 መፈጠሩ፣
• የወርቅ የወጪ ንግድ አፈጻጸም በኮንትሮባንድና ህገ ወጥ ንግድ መስፋፋት በጣም መቀነስ፣ የዘርፉን ትኩረት አቅጣጫ በመለየት አለመስራት፣
• የምርመራና የምርት ፈቃድ ወስደው ሥራ ያቆሙ ኩባንያዎች ወደስራ እንዲገቡ ማድረግ ላይ የተሰራ ስራ አናሳ መሆን፣
• በዘርፉ እያደገ የመጣውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ የክልል አመራሮችና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በትኩረት ያለመስራት
• በዘርፉ እየተስፋፋ የመጣውን የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ከክልል አመራሮችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ያለዉን ተቋማዊ ግንኙነት በማጠናከር ተጨባጭ ማሻሻያዎችን ማከናወን ያስፈልጋል
• የ2ኛዉ 100 ቀን አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የተቋሙ ዋና ዋና ሃላፊነቶች ላይ ያተኮሩ መለኪያዎችን ማካተትና በመረጃ የተደገፈ ሪፖርት ማቅረብ ላይ ክፍተቶች ታይተዋል። በመሆኑም የዘርፉን አፈጻጸም በተጨባጭና ዉጤት ተኮር በሆነ መልኩ የሚያሳዩ መለኪያዎችን ማካተትና በመረጃ የተደገፈ ሪፖርት ማቅረብ ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል
• የማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ የቁጥጥር ሥራን ሊያጠናክሩ የሚችሉና የዘርፉን ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችሉ አደረጃጀቶችን ከፌደራል እስከ ወረዳ ድረስ የመዘርጋት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል
• ዘርፉ ከልምድ አሰራር ሳይንሳዊ ወደ ሆነ አሰራር ለማምጣጥ እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ቢኖሩም አጥጋቢ አይደሉም፡፡ ስለሆነም በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል

የእርስዎ አስተያየት