የፕላንና ልማት ኮሚሽን

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የአስር ዓመት ሀገራዊ መሪ የልማት ፕላን ዝግጅት

100%

ሁሉንም የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ያካተተ የአስር ዓመት መሪ የልማት ፕላን ረቂቅ ለማዘጋጀት ታቅዶ የመጀመሪያ ረቂቅ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

የልማት ፕሮግራሞች/ፕሮጀክቶች አፈጻጸም ክትትልን ማጠናከር

75%

የልማት ፕሮጀክቶች አመራር እና አስተዳደር ደንብን በተገኙ ግብረ-መልሶች አዳብሮ ለጠቅላይ አቃቤ ህግ አቅርቧል።
የልማት ፕሮጀክቶች አመራር እና አስተዳደር ደንብን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ ረቂቅ መመሪያዎችን በተገኙ ግብረ-መልሶች የማጎልበት ስራ ተሰርቷል።

የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ዝግጅት

63%

የ2010 በጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ለማካሄድ ጅምር ስራዎች ተጠናቀዋል።
የ2011 በጀት ዓመት የተጠቃለለ የዘጠኝ ወራት የማክሮ ኢኮኖሚ የአፈጻጸም ግምገማ ሪፖርት ሰነድን ተዘጋጅቷል።

የብሔራዊ ኢኮኖሚ አካውንት ስታትስቲክስ ግምቶች ዝግጅት

58%

የ2011 የ 1ኛውን እና የ2ኛው ሩብ ዓመት የሀገር ውስጥ ምርት ግምት (QGDP - Supply side) በሙከራ ደረጃ ተዘጋጅቶ ቀርቧል።
የ2008 በጀት ዓመት የምርት አቅርቦትና አጠቃቀም ሚዛን ሠንጠረዥ (Supply and Use Table (SUT)) ሥራን አቅርቦትና አጠቃቀም ሚዛን ሠንጠረዥ አፈፃፀም ደረጃን 90 በመቶ እየተሰራ ነው።
ወጥ የሆነ የክልል ኢኮኖሚ አካውንት አዘገጃጀት ሥርዓት ለመዘርጋት የሚያስችል የስራ አካሄድ ረቂቅ የመነሻ ሀሳብ ሰነድ ዝግጀት በጅምር ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ሀገራዊ የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ሥርዓት ግንባታ

78%

የእድገትና ትራስንፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም የክትትልና ግምገማ መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ ማንዋልና ቼክ-ሊስቶችን እየተዘጋጁ ነው።
በአፈጻጸም ዙሪያ በቁልፍ የውጤት መስኮች (KRA) እና ቁልፍ የውጤት አመልካቾች (KPI) ላይ በመመስረት ተቋማት የሚገመገሙበትን አሰራር ለመዘርጋት ስራዎች እየተሰሩ ነው።

የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ አያያዝና አጠቃቀም ማጎልበት

95%

የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ አያያዝና አጠቃቀም የውስጥ መመሪያ በማጠናቀቅ ሥራ ላይ እንዲውል ተደርጓል። የቤተመጻሕፍት አውቶሜሽንና የኤሌክትሮኒክ ቤተመጻሕፍት ማደራጀት ሥራ የመጀመሪያ ምዕራፍ ስራ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል።

የሰው ሀብት አስተዳደርና አቅም ግንባታ

47%

ለኮሚሽኑ ባለሙያዎች በተለያዩ መስኮች የክህሎት ሥልጠና ተሰጥቷል። የኮሚሽን መ/ቤቱን የአደረጃጀት፣ የደመወዝ እና የጥቅማ ጥቅም ማሻሻያ ጥናት ማስጀመር ተችሏል።
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
• በዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ተጠያቂነትን ለማስፈን የመንግስት አስፈጻሚ አካላት ቁልፍ የውጤት አመልካቾች (KPI) ላይ በመመስረት አፈጻጸምን መለካት እንዲጀምሩ የተከናወኑ ስራዎች (የባለሙያዎች ስልጠናዎችን ጨምሮ) የሚበረታቱ ናቸዉ
• የመረጃና የመገናኛ ቴክኖሎጂ አያያዝና አጠቃቀም ማጎልበት ላይ የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱ ሲሆን የሴንትራል ስታትስቲክስ ባለስልጣን ላይ ያሉ የመረጃ ክፍተቶችን ማጠናከር በቀጣይነቱ ትኩረት ቢደረግ
• ወጥ የሆነ የክልል ኢኮኖሚ አካውንት አዘገጃጀት ሥርዓት ለመዘርጋት የታቀዱ ስራዎች ዘግይተዋል
• በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የ2010 በጀት ዓመት አፈፃፀም ላይ በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ከባለድርሻ አካላት ጋር የታቀደዉ ውይይት አልተካሄደም
• በተለያዩ የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፍ አፈጻጸም መለኪያዎች ላይ በመንግስት ተቋማት እንዲሁም በሌሎች አካላት ዘንድ ያለዉ መረጃ ወጥ ባለመሆኑ በየጊዜዉ ለተቋማትና ለህዝምብ ግልጽ የሚደረግ ወጥ የሆነና ተአማኒነት ያለዉ ብሄራዊ መረጃ ማቅረብ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ያስፈልጋል
• የአስፈጻሚ ተቋማትን አፈጻጸም ክትትል አስመልክቶ ለተለያዩ አካላት (ለፓርላማ፣ ለጠ/ሚኒስቴር ቢሮ፣ ለካቢኔ ወዘተ) የሚላኩ የእቅድና የሪፖርት ፎርማቶች ወጥ እንዲሆኑ ከተቋማትና ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት መስራት
• ሌሎች የመንግስት ተቋማት ስለ እቅድ አወጣጥ እና ሪፖርት በተመለከተ አቅም እንዲኖራቸው ከፕላን እና ልማት ኮሚሽን ቀጣይነት ያለውና ተጨባጭ ለዉጥ ማስገኘት የሚያስችል ድጋፍ የማድረግ ስርዓት ቢዘረጋ። ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በግልጽ በመወያየት የድጋፍ ስራዉን እነሱም በሃላፊነት እንዲቀበሉት ማድረግ ያስፈልጋል

የእርስዎ አስተያየት