የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ክለሳና አስተማማኝ የአካባቢና የቀጠና ሠላምና ውህደት

80%

የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ክለሳ ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጀቷል
ከኤርትራ ግንኙነት ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖረው ክትትል ማድረግ ታቅዶ የሚኒስትሮች ምክከር፣ የጋራ ኮሚሽኑ ስምምነትና ጥናት ተፈጽሟል

አገራዊ እና ተቋማዊ ለውጥ ማስቀጠል

50%

በተለያዩ አገራት፣ አህጉራዊ እና አለምአቀፋዊ ድርጅቶች በኩል ተገቢውን ድጋፍ ለማስገኘት ታቅዶ ከ28 አገሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር የድጋፍ ጥያቄና ከአጋሮች የሸገር ማስዋብ ፕሮጀክት ለመደገፍ ቃል መገባቱ

ሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር አጋሮችን ማበራከት

63%

የሁለትዮሽ ስምምነቶች ከፈረንሳይ፣ ከኡራጓይ፣ ከኮሪያ እና ከጃፓን ጋር መፈራረም ታቅዶ ወደ 16 የተለያዩ ስምምነቶች መፈረማቸው

ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አጠናክሮ መቀጠል

73%

የስራ ስምሪትን ህጋዊ ማድረግና የዜጎቻችንን መብት በማስጠበቅ ረገድ 10,491 ከእስር መፈታት፣ 39,408 ከስደት መመለስ ተደርሷል

የውጭ ሀብት ፍሰትን ማጠናከር እና የልማት አጋርነትን ማጎልበት

92%

የወጭ ኢንቨስትመንት ዙሪያ 21 የቢዝነስ ፎረሞችን፣ ለ 3 ትላልቅ እና 222 የአነስተኛና መካከለኛ ኩባንያዎች የቅድመ ኢንቨስትመንት ጉብኝት፣ ከውጭ ባለሃብቶች ጋር ሽርክ ታቅዶ 48 የቢዝነስ ፎረሞችን፣ 279 የአነስተኛና መካከለኛ ኩባንያዎች የCMG የJV ተነሳሽነት መታየቱ

ብድርን ማሰረዝ፣ የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘም እና አዳዲስ የድጋፍ ምንጭ ማፈላለግ

100%

እርዳታ፣ ብድር ስምምነት ፕሮጀክቶች ዙሪያ ተገቢ ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ ታቅዶ ስዊድን 20 ሚሊዮን ድጋፍ ስምምነት፣ ዴንማርክ 4.5 ሚልዮን ዶላር የድጋፍ ስምምነት፣ የአሜሪካ 337 ሚልዮን ዶላር ብድርና ድጋፍ ስምምነት ተደርጓል.

ተቋም ብክነትን የሚቀንሱ እርምጃዎችን መውሰድ

83%

የ2011 የበጀት ድልድል ማድረግ ታቅዶ ስራ ተጀምሯል

ዲፕሎማቲክ ማዕከልነት ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ማሳደግ

67%

በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤምባሲዎች በተደጋጋሚ ለሚያቀርቡት የመሬት ጥያቄ መፍትሄ መሰጠት ዙሪያ ከአ.አ. በመሬት ነክ ጉዳዮች መልስ ማግኘት ተችሏል

ምቹ የሆነ የስራ ቦታ መፍጠር

63%

ምቹ የሆነ የስራ ቦታ መፍጠር ዙሪያ፣ የግቢ ማስዋብ ስራ መጠናቀቅ ታቅዶ ስራዉ ተጀምሯል

የሲቪል ሰርቪሱን ሪፎርም

70%

ከደረጃ ዕድገትና ደምወዝና ጥቅማ ጥቅም ጋር ያልተመለሱ ጥያቄዎችን ለመመለስ ጥናት ሰነድ እየተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ለአመራር ይቀርባል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች

•የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ክለሳ ረቂቅ ሰነድ ተዘጋጀቷል
• በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ከ10ሺህ በላይ ዜጎችን ከእስር ማስፈታት መቻሉ

•የዳያስፖራ ኤጀንሲን ስራ ማስጀመር ታቅዶ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም
•በድንበር ጉዳይና በተፋሰስ ጉዳይ ላይ ጥናቶችንና ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ የማድረግ ስራዎች ታቅደው የተወሰኑ ስራዎች ብቻ ነው የተፈጸፀሙት

•የኤምባሲዎች የአሰራርና የመረጃ ወጥነት ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎች ለሚቀጥለው የ100ቀን እቅድ ላይ መካተት አለባቸው
•የሚኒስቴር መ/ቤቱ የprofessionalism አቅም ማጎልት ዙሪያ የበለጠ ስራዎች መስራት አለበት
•ወደፊት የ100 ቀን እቅድ ላይ ትኩረት ዘርፎች ላይ (ማለትም በቱሪዝም፣ በጤና፣ በትምህርት እና የመሳሰሉትን) ባንጸባረቀ መልኩ ቢተገብር
•አንዳንድ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ስራ quantifiable ለማድረግ ቢያስቸግርም፣ በተቻለው ጥረት የሪፖርት አደራረግ ስልት ላይ የበለጠ የሚለኩ እና ግብ ተኮር በማድረግ ላይ ቢሰራ። ለዚህም እንዲረዳው ትኩረት ያላቸው የአፈጻጸም መለኪያ አተገባበሮች ላይ ትኩረት ቢሰጥ
•የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ረቀቅ እንደተጠናቀቀ፣ ያለውን ፋይዳ እና አተገባበር ዙሪያ ትኩረት በመስጠት ግልጽ እቅድ ማካተት

የእርስዎ አስተያየት