Home 100 Days Performance Report
ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡
የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታና ጥገና |
67% |
---|---|
የ840 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታ እና የ4,910 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ማድረግ ታቅዶ የ452 ኪ.ሜ ግንባታ እና የ2604 ኪ.ሜ መንገድ ላይ ጥገና ማድረግ ተችሏል | |
የድሬዳዋ ደወሌን አዲስ የክፍያ መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ ታቅዶ የአፈጻጸም የቅድመ ዝግጀት ስራ እየተሰራ ነው |
የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ |
58% |
---|---|
በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር የእርማት ስራ አፈጻጸም አሁን ካለበት 80% ወደ 100% በማድረስ ለማጠናቀቅ ታቅዶ የማስተካከያ ከሚያስፈልጋቸው ግኝቶች ውስጥ አንገብጋቢ የሆኑትን የመለየት ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹን ማስተካከል ተችሏል |
የመንገድ ትራንስፖርትና የባቡር አገልግሎት |
86% |
---|---|
በመናሃሪያዎች የተጓጓዥ የህዝብ ቁጥርን ወደ 25 ሚሊዮን ማሳደግና፤ የቀላል ባቡር በሰሜን - ደቡብ እና በምስራቅ - ምዕራብ አቅጣጫ ጣቢያዎች ላይ የሚደርስበትን ደቂቃ ከ15 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ማድረስ ታቅዶ ደቂቃ 12 ወደ ተቀንሷል፣ 25.3 ሚሊዮን ተጓዥ ህዝብ ደርሷል |
የአዲስ አበባን ትራንስፖርት አገልግሎት ማሻሻል |
69% |
---|---|
በአ.አ ቀላል ባቡር ተጓዥ የነበረውን ምልልስ ወደ 120 ሺ ማድረስና አዳዲስ አውቶብሶች ግዢን 334 ማድረስ ታቅዶ 273 አውቶብሶችና 115,739 ተጓዥ ተደርሷል |
የሎጀስቲክስ ውጤታማነት |
78% |
---|---|
የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ማዕከል ያደረገ የሎጀስቲክ ወጪን በ5% መቀነስ ታቅዶ በ10% ተቀንሷል | |
የብትን ጭነት አገባብ 950,000 ቶን ጭነት ታቅዶ 23,000 ቶን ገብቷል |
አቪዬሽንን ማሻሻል |
80% |
---|---|
ICAO ምዘናን ከ73% ወደ 85% ማድረስ ታቅዶ 80% ማድረስ ተችሏል |
የጎለበተ ቅንጅታዊ አሰራር እና ምቹ የስራ አካባቢ |
100% |
---|---|
ከተጠሪ ተቋማትና ከክልሎች ጋር አብሮ የማቀድ፣ የመገምገም እና የመደጋገፍ ስርዓትን ማጠናከርና የኤርጎኖሚክስ ስራ ደረጃ በደረጃ ማጠናቀቅ ታቅዶ ተተግብሯል |
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ | ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ | ቀጣይ አቅጣጫዎች |
---|---|---|
• የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ማዕከል ያደረገ ቀልጣፋና ውጤታማ የትራንዚት ትራንስፖርት ስርዓትን ከማረጋገጥ አንጻር የሎጀስቲክ ወጪን በ10 በመቶ መቀነስ ተችሏል • የአዲስ አበባን ቀላል ባቡር በሰሜን - ደቡብ እና በምስራቅ - ምዕራብ አቅጣጫ ጣቢያዎች ላይ የሚደርስበትን ደቂቃ ከ15 ወደ 12 ደቂቃ ማድረስ ተችሏል • በሚኒስቴር መ/ቤቱ ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር የተሰሩ የቢሮ ማስዋብ ስራዎች ይበረታታሉ |
• የዲሜሬጅ ህግ አፈፃፀምን ከ 89 % ወደ 100% ማድረስ፣ የትራንዚት ምልልስን በ11% መጨመርና የትራንስፖርት ዋጋን በኩንታል 5% መቀነስ ታቅዶ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ ነው • የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ዙሪያ የታቀዱ በርካታ ግቦች አልተሳኩም |
▪ የሎጅስቲክስ ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዳዲስ ኢንቨስመንት መሳብና የግል ዘርፉ ተሳታፊት ዙሪያ መስራት
▪በኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር ጭነትን በማሳደግና ሌሎች የማስተካከያ ስራዎችን በመስራት መስመሩ ዉጤታማ እንዲሆን ማስቻል ▪ የሀገሪቷን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ዙሪያ በበለጠ መልኩ መስራት (ለምሳሌ የሳይክል ትራንስፖርት፣ አዳዲስ መስመሮች መክፈት፣ ተጨማሪ አውቶቢሶች መመደብ፣ የትራፊክ ማኔጅመንት ሲስተምን ማሻሻል፣ ወዘተ) ▪የመንግስት መ/ቤቶችን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ በመንግስት መኪናዎች የuber ሰርቪስ የመስጠት ዙሪያ ጥናት ቢያካሂድ ▪ በዲመረጅ ህግ ዙሪያ የሚታዩትን ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በበለጠ በመቀናጀት የተጠናከረ ስራ መስራት |