የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የቅርሶች ጥበቃና ጥገና ሥራ ማጠናከር

55%

ላሊበላ የጥገና እና መጠለያ ማንሳት ፕሮጀክት ሰነዱን አጠናቆ ለፊርማ ማዘጋጀት ታቅዶ የሚያስፈልገዉ ዝግጅት ተደርጎ የፋይናንስ ስምምነትም ከፈረንሳይ ጋር ተፈርሟል
የአክሱም ቁጥር 3 የጥገና ፕሮጀክት ሥራ ማስጀመር ታቅዶ በአማካሪዉ የተዘጋጀው ቢል ኦፍ ኳንቲቲ ለዩኔስኮ በድጋሚ ተልኮ መልስ እየተጠበቀ ነዉ። ጅማ አባጅፋር ሜሰነሪ/የግንብ ጥገና ሥራ ማጠናቀቅ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አሁንም የቅድመ ዝግጅት ስራ ላይ ይገኛል
በቅርስ ጥገና ላይ የግል ዘርፉ እንዲሳተፍ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ዉይይቶች የተደረጉ ቢሆንም ተጨባጭ ውጤቶች አልተገኙም

በኪነጥበቡ ዘርፍ ያሉበትን ማነቆዎችን መፍታት

76%

የግል ባለሃብቱ ኪነጥበቡን እንዲደግፍ ለማድረግ ታቅዶ የአርት ፈንድ ለማቋቋም ሥራ ተጀምሯል። አስፈላጊ የሆነ የኪነጥበብ ማበረታቻዎችን ለኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቀርበዋል
የተለያዩ ኪነጥበብ ስራዎችና የሉሲ ለሰላምና ለፍቅር ጨምሮ በ4 ክልሎች ማቅረብ ተችሏል

በዘርፉ የሚሰማራውን የሰው ኃይልና አጠቃላይ የእሴት ሰንሰለቱን የተጠናከር ማድረግ

69%

ብዛት ይላቸዉ የስልጠና እቅዶች ተይዘዉ የነበሩ ሲሆን ~75% አፈጻጸም ነበረዉ
ለ70 አዳዲስ ሆቴሎች ደረጃ ምደባ ለመስጠት ታቅዶ ለ90 ተቋማት ተከናዉኗል
በአገሪቱ ያሉ የቱሪዝም ሀብቶችን መረጃ ማሰባሰብና ማደራጀት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አፈጻጸም አላሳየም

የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ማስፋፋት

62%

የአገር ውስጥ ቱሪዝም ለማስፋፋት ስትራቴጂ ማጸደቅና ንቅናቄ ለመፍጠር እቅድ ተይዞ ስትራቴጂዉ ተጠናቆ ዉይይት ላይ ሲሆን ንቅናቄ መፍጠርን በተመለከተ ግን ከቅድመ ዝግጅት የዘለለ ተጨባጭ ስራ አልተከናወነም

የስፖርት ዘርፉ ያለዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሚና ማጠናክር

77%

መንግስታዊ የስፖርት አደረጃጀቶችን የቅንጅታዊ አሰራር የሚመራ ሰነድ ማዘጋጀት ታቅዶ ተግባራዊ ተደርጓል
ለ31 የመንግስት ተቋማት የስፖርት ኮሚቴ እንዲያቋቁሙ ጥያቄ ቀርቦ ከዚያ ውስጥ እስከሁን 25 አቋቁመዋል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች

•በኪነጥበብና በስፖርት ዘርፉ ንቅናቄ ለመፍጠር የተከናወኑ ስራዎችና ከተለያዩ ተቋማትና የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የተጀመረዉ የቅንጅት አሰራር የሚበረታታ ነዉ
•ምቹ የስራ ሁኔታ በመፍጠርም ረገድ የሚበረታታ የእድሳት ስራ ተጀምሯል
•‹‹ጉዞ ሉሲ ለሰላም›› ፕሮጀክት ጋር እስከአሁን በአራት ክልሎች መካሄዱ

•የቅርሶች (የላሊበላ፣ አክሱምና አባጅፋር) ጥገና የዘገየ አፈጻጸም ያሳየ በመሆኑ ተጠናክሮ መሰራት አለበት
•የቱሪዝም መረጃ የተቀናጀና ተአማኒነት ያለዉ ባለመሆኑና ይህንንም አስመልክቶ የተጀመረዉ ስራ አፈጻጸሙ አነስተኛ ነዉ
•ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ስራው አነስተኛ መሆኑ
•የስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እና የመረጃ ስርዓት አለመዘመን

•ቅርሶችን የማሳደስ ሰራዉ አፈጻጸም አነስተኛ በመሆኑ በሚቀጥለዉ የ100 ቀን እቅድ ላይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት ተጨባጭ ዉጤት ለማስገኘት ቢሰራ። ለዚህ ስራ የሚሆነዉ በጀት በአብዛኛዉ ከዉጭ የሚገኝ በመሆኑ ስራዉን ሊያዘገይ እንደሚችል የምንገነዘብ ቢሆንም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ያሚደረገዉን ክትትልና ድርድር በማጠናከር እድሳቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ። በተጨማሪም የግል ዘርፉ በእድሳት ሰራዉ ላይ የሚሳተፍበትን አግባብ መቀየስ
•በሃገሪቷ የቱሪዝም መረጃ የተቀናጀና ተአማኒነት ያለዉ ባለመሆኑ ተቋሙ ይህንን ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባትና ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ችግሩን ለመፍታተ በትኩረት ቢሰራ
•ለቀጣይ ፕሮጀክቶች የልምድ መማሪያ እንዲሆን በቅርቡ የሚጠናቀቀዉን የቤተ-መንግስት እድሳት ፕሮጀክት እየተሰራ/እየታደሰ ያለበትን አግባብ ማጥናት። እንዲሁም ቀጣይ አዳዲስ ፕሮጀክቶች (ለምሳሌ የአአ ወንዞች ፕሮጀክት፣ ለገሃር ፕሮጀክት፣ ቀጣዩ የቤተመንግስት እድሳት፣ ጎተራ- ሳር ቤት) ላይ በማተኮር የሚያስፈልገዉን ድጋፍ ማድረግ

የእርስዎ አስተያየት