የትምህርት ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የትምህርት ፍኖተ ካርታ ዝግጅትና ትግበራ

90%

የ15 ዓመት የትምህርት ፍኖተ ካርታ የመተግበሪያ ዝርዝር መርሃግብር ዝግጅት ተጠናቋል
በፍኖተ ካርታ ጥናት ላይ የተመሰረተ ቅድመ ረቂቅ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተዝጋጅቷል

የትምህርት ጥራትና አግባብነትን በየደረጃው ማረጋገጥ

78%

በ4012 ት/ቤቶች መረጃ በመሰብሰብና በመተንተን የተማሪዎች ዝቅተኛ መማር ብቃት (MLC) መለካትና የመረጃ ማረጋገጥ ስራ ታቅዶ ተጠናቋል
ለ 8,370 የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ የእንግሊዝኛ ቋንቋ መምህራን የክህሎትና የማስተማር ሥነ ዘዴ ስልጠና ሊስጥ ታቅዶ ለ3,427 ተሰጥተዋል

ብቁ ዜጋ ማፍራት

67%

የተግባር ተኮር ጎልማሶች ትምህርት ስትራተጂ እስኪጸድቅ እየተጠበቀ ነው
የትምህርት ሂደቱን የሚያስተጓጉሉ አዋኪ ሁኔታዎች ያሉበትን ሁኔታ በመዳሰስ ዘላቂ የመፍትሄ ሃሳቦች የያዘ አንድ ሰነድ በከፊል ተጠናቋል

የትምህርት ተሳትፎና ብቃት ማጠናከር

60%

የት/ቤቶች ምገባ ፕሮግራም በተመረጡ ስምንት ክልሎች ለ 880,806 ተማሪዎች በመስጠት ታቅዶ ተከናውኗል
የግል የትምህርት ተቋማትን ለማበረታታት የችግር መለያ አገር አቀፍ አውደጥናት እንዲካሄድ ታቅዶ ቅድመ ዘግጅት ላይ ነው

የአቅም ግንባታ ስራዎች ማከናወን

67%

ለ 30 መካከለኛ አመራር በዘመናዊ የሰው ሃብት፣ የሎጂስቲክስ እና የሃብት አስተዳደር የታቀደ ስልጠና እንዲሰጥ ታቅዶ ተጠናቋል

አይ.ሲ.ቲን ለትምህርት ልማት ማዋል

50%

ሁለት የት/ሚ/ር ተጠሪ ተቋማት (የፈተናዎች ድርጅትና የ አይ.ሲ.ቲ. ማእከል) ወደ ዘመናዊ የቢሮ አሰራር እንዲገቡ ሊደረግ ታቅዶ የአደረጃጀት መዋቅር እና ሬኖቬሽን ስራ ተጀምሯል

የክትትል፣ የድጋፍና የግንኙነት ስርዓት ማጠናከር

78%

የትምህርት ጥራት ማረጋጫ ፓኬጅና የሌሎች ፕሮጀክቶች ግቦች በተያዘላቸው መርሃግብር መሰረት እንዲጠናቅቁ በእቅዱ መሰረት እየትካሄደ ነው
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
•የ15 ዓመት የትምህርት ፍኖተ ካርታ የመተግበሪያ ዝርዝር መርሃግብር ዝግጅት ተጠናቋል
• በፍኖተ ካርታ ጥናት ላይ የተመሰረተ ቅድም ረቂቅ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተዘጋጅቷል

•የ2012 ትምህርት ዘመን የተማሪ ተሳትፎን ለማሳደግ የሚረዱ ተጨማሪ ት/ቤቶች በህብረተሰብ ተሳትፎ ለመገንባት የሚያስችል እቅድ እንዲዘጋጅ ታቅዶ ስራው በሚጠበቀው ፍጥነት እየሄደ አይደለም

•የፍኖተ ካርታውን መሰረት ያደረገው የትምህርት ፖሊሲ ወደ ትግበራ በሚገባበት ጊዜ ከፍተኛ ዝግጅትና ጥንቃቄ ቢደረግ። ተያይዞም ትግበራውን በተመለከተ ለተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት በቂ ግንዛቤ ለመፍጠር ትኩረት ተሰጥቶት ቢሰራበት
•የትምህርት ጥራትን በተመለከተ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመሩት ጥናቶች አበረታች ቢሆንም ዋና ዋና ማነቆዎችን አውጥቶ መፍትሔዎችን ማበጀት ተገቢ ነው

የእርስዎ አስተያየት